15 ልጄ ሆይ፤ ልብህ ጠቢብ ቢሆን፣የእኔም ልብ ሐሤት ያደርጋል፤
16 ከንፈሮችህ ትክክሉን ቢናገሩ፣ውስጣዊ ሁለንተናዬ ሐሤት ያደርጋል።
17 ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ነገር ግን ዘወትር እግዚአብሔርን ለመፍራት ትጋ።
18 ለነገ ርግጠኛ አለኝታ ይኖርሃል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።
19 ልጄ ሆይ አድምጥ፤ ጠቢብም ሁን፤ልብህም ከትክክለኛው መንገድ አይውጣ።
20 ብዙ የወይን ጠጅ ከሚጠጡ፣ሥጋ ከሚሰለቅጡ ጋር አትወዳጅ፤
21 ሰካራሞችና ሆዳሞች ድኾች ይሆናሉና፤እንቅልፋምነትም ቡትቶ ያለብሳቸዋል።