13 በመከር ጊዜ የበረዶ ቅዝቃዜ ለሰስ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ታማኝ መልእክተኛም ለላኩት እንደዚሁ ነው፤የጌቶቹን መንፈስ ያሳርፋልና።
14 የማይለግሰውን ስጦታ እቸራለሁ ብሎ ጒራ የሚነዛ ሰው፣ዝናብ እንደሌለው ደመናና ነፋስ ነው።
15 በትዕግሥት ገዥን ማግባባት ይቻላል፤ለስላሳ አንደበትም ዐጥንት ይሰብራል።
16 ማር ስታገኝ በልክ ብላ፤ከበዛ ያስመልስሃል።
17 ወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ፤ታሰለቸውና ይጠላሃል።
18 በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር፣እንደ ቈመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ተሳለ ፍላጻ ነው።
19 በመከራ ጊዜ በወስላታ ሰው መተማመን፣በተበላሸ ጥርስና በሰለለ እግር እንደ መታመን ነው።