12 ጥንቁቅ አደጋን አይቶ ይሸሸጋል፤ማስተዋል የጐደለው ግን ወደዚያው ይሄዳል፤ ይጐዳልም።
13 ለማይታወቅ ሰው የተዋሰን ልብሱን ግፈፈው፤ለዘልዛላ ሴት ከተዋሰማ አግተው።
14 ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን በማለዳ ቢመርቅ፣እንደ ርግማን ይቈጠራል።
15 ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥጠፈጠፍ ናት፤
16 እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትንበእጅ እንደ መጨበጥ ነው።
17 ብረት ብረትን እንደሚስል፣ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።
18 በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል።