5 የተገለጠ ዘለፋ፣ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።
6 ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣የወዳጅ ማቊሰል ይታመናል።
7 ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።
8 ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ጎጆዋን ለቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።
9 ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።
10 የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።
11 ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሰኘው፤ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።