1 ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው።
2 አገር ስታምፅ፣ ገዦቿ ይበዛሉ፤አስተዋይና ዐዋቂ ሰው ግን ሥርዐትን ያሰፍናል።
3 ድኾችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ሰብል እንደሚያጠፋ ኀይለኛ ዝናብ ነው።
4 ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።