2 ጻድቃን ሥልጣን ሲይዙ ሕዝብ ሐሤት ያደርጋል፤ክፉዎች ሲገዙ ግን ሕዝብ ያቃስታል።
3 ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤የአመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።
4 ፍትሕን በማስፈን ንጉሥ አገርን ያረጋጋል፤ጒቦ ለማግኘት የሚጐመጅ ግን ያፈራርሳታል።
5 ባልንጀራውን የሚሸነግል፣ለገዛ እግሩ መረብ ይዘረጋል።
6 ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።
7 ጻድቅ ለድኾች ፍትሕ ይጨነቃል፤ክፉ ሰው ግን ደንታ የለውም።
8 ተሳዳቢዎች ከተማን ያውካሉ፤ጠቢባን ግን ቊጣን ያበርዳሉ።