22 ባሪያ ሲነግሥ፣ሰነፍ እንጀራ ሲጠግብ፣
23 የተጠላች ሴት ባል ስታገባ፣ሴት ባሪያ በእመቤቷ እግር ስትተካ።
24 “በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንንሽ ናቸው፤ሆኖም እጅግ ጠቢባን ናቸው፤
25 ጒንዳኖች ደካማ ፍጡራን ናቸው፤ሆኖም ምግባቸውን በበጋ ያከማቻሉ።
26 ሽኮኮዎች ዐቅመ ደካማ ናቸው፤ሆኖም መኖሪያቸውን በቋጥኞች መካከል ይሠራሉ፤
27 አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ሆኖም ቅደም ተከተል ይዘው ይጓዛሉ፤
28 እንሽላሊት በእጅ ትያዛለች፤ሆኖም በቤተ መንግሥት ትገኛለች።