3 ጒልበትህን በሴት አትጨርስ፤ብርታትህንም ነገሥታትን ለሚያጠፉ አታውል።
4 “ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤
5 አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፋሉ።
6 ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤
7 ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።
8 “ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።
9 ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”