1 ልጄ ሆይ፤ ጥበቤን ልብ በል፤የማስተዋል ቃሌንም በጥሞና አድምጥ፤
2 ይህም ልባምነትን ገንዘብ እንድታደርግ፣ከንፈሮችህም ዕውቀትን እንዲጠብቁ ነው።
3 የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ያንጠባጥባልና፤አንደበቷም ከቅቤ ይለሰልሳል፤
4 በመጨረሻ ግን እንደ እሬት ትመራለች፤ሁለት አፍ እንዳለውም ስል ሰይፍ ትሆናለች።
5 እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፤ርምጃዎቿም በቀጥታ ወደ ሲኦል ያመራሉ።
6 ስለ ሕይወት መንገድ ደንታ የላትም፤መንገዶቿ ዘወርዋራ ናቸው፤ ለእርሷ ግን አይታወቃትም።
7 እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ከምነግራችሁ ቃል ፈቀቅ አትበሉ።