1 ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ጠብቅ፤ትእዛዜንም በውስጥህ አኑር።
2 ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው።
3 በጣትህ ላይ እሰረው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው።
4 ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤