5 ከአመንዝራ ሴት፣በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ሴት ይጠብቁሃል።
6 በቤቴ መስኮት፣በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።
7 ማስተዋል የጐደለውን ወጣት፣ብስለት ከሌላቸው መካከል አየሁት፤ከጎልማሶችም መካከል ለየሁት።
8 የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤
9 ቀኑ መሸትሸት ሲል፣በውድቅት ሌሊት፣ በጽኑ ጨለማ።
10 ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤እንደ ዝሙት አዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ።
11 ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤እግሮቿ አርፈው ቤት አይቀመጡም፤