22 እግዚአብሔር ከቀድሞ ሥራዎቹ በፊት፣የተግባሮቹ መጀመሪያ አድርጎ አመጣኝ፡
23 ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ፣ከጥንት ከዘላለም ተሾምሁ።
24 ከውቅያኖሶች በፊት፣የውሃ ምንጮች ከመፍለቃቸው በፊት ተወለድሁ፤
25 ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፣ከኰረብቶችም በፊት ተወለድሁ፤
26 ምድርን ወይም ሜዳዎቿን፣ወይም ምንም ዐይነት የዓለም ትቢያን ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ።
27 ሰማያትን በዘረጋ ጊዜ፣በውቅያኖስ ላይ የአድማስ ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፤
28 ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፣የውቅያኖስን ምንጮች በመሠረተ ጊዜ፣