4 “ሰዎች ሆይ፤ የምጠራውኮ እናንተን ነው፤ለሰው ልጆች ሁሉ ድምፄን ከፍ አደርጋለሁ።
5 እናንተ ብስለት የጐደላችሁ፤ ጠንቃቃነትን ገንዘብ አድርጉ፤እናንተ ተላሎች፤ ማስተዋልን አትርፉ።
6 የምናገረው ጠቃሚ ነገር ስላለኝ አድምጡኝ፤ቀና ነገር ለመናገር ከንፈሮቼን እከፍታለሁ።
7 አንደበቴ እውነትን ይናገራል፤ከንፈሮቼ ክፋትን ይጸየፋሉና።
8 ከአንደበቴ የሚወጡት ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤አንዳቸውም ጠማማና ግራ የሚያጋቡ አይደሉም።
9 በጥልቅ ለሚያስተውሉ ሁሉም ቀና ናቸው፤ዕውቀት ላላቸውም ስሕተት የለባቸውም።
10 ከብር ይልቅ ምክሬን፣ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ፤