9 “ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፤እማርካቸዋለሁ፤ምርኮን እካፈላለሁ፤ነፍሴ በእነርሱ ትጠግባለች፤ሰይፌን እመዛለሁ፤እጄም ትደመስሳቸዋለች አለ።
10 አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ባሕርም ከደናቸው፤በኀያላን ውሆች፣እንደ ብረት ሰጠሙ።
11 “አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ከአማልክት መካከል፣ እንደ አንተ ማን አለ?በቅድስናው የከበረ፣በክብሩ የሚያስፈራ፣ድንቆችን የሚያደርግ፣እንደ አንተ ማን አለ?
12 ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ምድርም ዋጠቻቸው።
13 ‘በማይለወጠው ፍቅርህ፣የተቤዥሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤እነርሱን በብርታትህ፣ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ።
14 አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል።
15 የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤የሞአብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ።