17 ሁለት ጉጦችም ጎን ለጎን ይሁኑለት፤ የማደሪያውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚሁ መልክ አብጅ
18 ለማደሪያው ድንኳን ክፍል ሃያ ወጋግራዎችን ሥራ።
19 ከሥራቸው የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ፤ በእያንዳንዱ ጒጠት ሥር አንድ መቆሚያ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ።
20 በሌላው ጎን፣ ከማደሪያው ድንኳን በስተ ሰሜን በኩል ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ፤
21 በእያንዳንዱም ወጋግራ ሥር ሁለት ሁለት መቆሚያ ሆኖ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ።
22 በዳር በኩል ለሚገኘው ይኸውም በምዕራብ ጠርዝ ላለው የማደሪያው ድንኳን ስድስት ወጋግራዎች አብጅ።
23 ዳርና ዳር ላሉት ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎች አብጅ።