16 ርዝመቱ አንድ ስንዝር፣ ስፋቱ አንድ ስንዝር ሆኖ ባለ አራት ማእዘንና በድርቡ የታጠፈ ይሁን።
17 ከዚያም በላዩ ላይ በአራት ረድፍ የከበሩ ድንጋዮች አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርዲዮን፣ ቶጳዝዮን፣ የሚያበረቀርቅ ዕንቁ፤
18 በሁለተኛውም ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር፣ አልማዝ፤
19 በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤
20 በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጴድ አድርግበት፤ በወርቅ ፈርጥም ክፈፋቸው።
21 የዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስሞች እንደ ማኅተም የተቀረጸባቸው ለእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ይሁኑ።
22 “ለደረት ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ ሆኖ የተጌጠ ጒንጒን አብጅለት።