1 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ፤ ከኀያሉ እጄ የተነሣ እንዲሄዱ፣ ይለቃቸዋል፤ ከኀያሉም እጄ የተነሣ ከአገሩ ያስወጣቸዋል” አለው።
2 እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።
3 ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤሎሂም) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም።
4 በእንግድነት የሚኖሩባትን የከነዓንን ምድር እንድሰጣቸው ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ።
5 ደግሞም በግብፃውያን ሥር በባርነት ሆነው ያሰሙትን የእስራኤላውያንን የሥቃይ ድምፄ ሰምቻለሁ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ።