26 ባሪያም ይሁን ነጻ ዜጋ፣ በእስራኤል የሚኖር ሁሉ እንዴት እጅግ ይሠቃይ እንደ ነበር እግዚአብሔር አየ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም።
27 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የእስራኤልን ስም ከምድረ ገጽ እንደሚያጠፋ ስላልተናገረ፣ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም አማካይነት ታደጋቸው።
28 በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ነገር፣ የፈጸመው ሁሉና ያደረጋቸው ጦርነቶች እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩትን ደማስቆንና ሐማትን እንዴት ለእስራኤል እንዳስመለሰ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?
29 ኢዮርብዓም ከአባቶቹ ከእስራኤል ነገሥታት ጋር አንቀላፋ፤ ልጁ ዘካርያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።