1 በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እግዚአብሔር፣ ‘ትሞታለህ ከእንግዲህ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል’ ብሎሃል” አለው።
2 ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤
3 “እግዚአብሔር ሆይ፤ በታማኝነትና በፍጹም ልብ በፊትህ እንደሄድሁ፣ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ አስብ፤” ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።
4 ኢሳይያስ የመካከለኛውን አደባባይ አልፎ ከመሄዱ በፊት የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤