1 እንግዲህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተዋቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በፍጹም! እኔ ራሴ ከብንያም ነገድ፣ የአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ።
2 እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። ኤልያስ በእስራኤል ላይ ክስ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንዳቀረበ፣ መጽሐፍ ስለ እርሱ ምን እንደሚል አታውቁምን?
3 “ጌታ ሆይ፤ ነቢያትህን ገድለዋል፤ መሠዊያዎችህን አፍርሰዋል፤ እኔም ብቻዬን ቀረሁ፤ ሊገድሉኝም ይፈልጋሉ።”
4 እግዚአብሔር የሰጠው መልስ ግን ምን ነበር? “ለበኣል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለራሴ አስቀርቻለሁ።”
5 በአሁኑ ጊዜም እንደዚሁ በጸጋ የተመረጡ ትሩፋን አሉ።
6 እንግዲህ በጸጋ ከሆነ በሥራ አይደለም፤ በሥራ ቢሆንማ ኖሮ ጸጋ፣ ጸጋ መሆኑ በቀረ ነበር።