3 መጽሐፍስ ምን ይላል? “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።”
4 አንድ ሰው ሥራ ከሠራ ደመወዙ እንደ ስጦታ ሳይሆን እንደ ተገቢ ዋጋው ይቈጠርለታል።
5 ነገር ግን ለማይሠራው፣ ኃጥኡን ሰው ጻድቅ በሚያደርግ በእግዚአብሔር ለሚያምን ሰው፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል።
6 ዳዊትም ጽድቅ ያለ ሥራ ስለሚቈጠርለት ሰው ብፅዕና እንዲህ ብሎአል፤
7 “መተላለፋቸው ይቅር የተባለላቸው፣ኀጢአታቸው የተሰረየላቸው፣ብፁዓን ናቸው።
8 ኀጢአቱን፣ ጌታ ከቶ የማይቈጥርበት ሰውብፁዕ ነው።”
9 ይህ ብፅዕና ለተገረዙት ብቻ ነው ወይስ ላልተገረዙትም? የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት ብለናል።