1 ነገሥት 11:35-41 NASV

35 መንግሥትን ከልጁ እጅ እወስዳለሁ፤ ለአንተም ዐሥሩን ነገድ እሰጥሃለሁ።

36 ስሜ እንዲኖርባት በመረጥኋት በዚያች በኢየሩሳሌም ከተማ ለባሪያዬ ለዳዊት ምንጊዜም በፊቴ መብራት እንዲኖረው፣ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጣለሁ።

37 አንተን ግን እኔ እወስድሃለሁ፤ ልብህ በወደደው ሁሉ ላይ ትነግሣለህ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ትሆናለህ።

38 ባሪያዬ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ አንተም ያዘዝሁህን ሁሉ ብትፈጽም፣ በመንገዴ ብትሄድ፣ ሥርዐቴንና ትእዛዜን በመጠበቅ ትክክል የሆነውን ነገር በፊቴ ብታደርግ፣ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ የዳዊትን ሥርወ መንግሥት እንዳጸናሁ፣ ለአንተም አጸናልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጣለሁ።

39 ከዚህ የተነሣም የዳዊትን ቤት አዋርዳለሁ፤ ነገር ግን ለዘላለም አይደለም።’ ”

40 ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ፈለገ፤ ኢዮርብዓም ግን ወደ ግብፅ ሸሸ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሺሻቅ ሄዶ፣ ሰሎሞን እስኪሞት ድረስ በዚያው ተቀመጠ።

41 የቀረው በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት የተከናወነው፣ የሠራውም ሁሉ፣ ጥበቡም በሰሎሞን የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎ የለምን?