1 ነገሥት

ምዕራፎች 4

መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሰሎሞን ሹማምት

1ንጉሥ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ 2ዋና ዋናዎቹ ሹማምቱም እነዚህ ነበሩ፤የሳዶቅ ልጅ ዓዛርያስ፣ ካህን፤ 3የሺሻ ልጆች ኤሊሖሬፍናአኪያ፣ ጸሓፊዎች፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣ ታሪክ ጸሓፊ፤ 4የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ የሰራዊቱ ዋና አዛዥ፤ሳዶቅና አብያታር፣ ካህናት፤ 5የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃገዦች የበላይ ኀላፊ፤የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡየቅርብ አማካሪ፤ 6አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራተቈጣጣሪ። 7እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ። 8ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ቤንሑር፣ በኰረብታማው በኤፍሬምምድር፤ 9ቤንጼቄር፣ በማቃጽ፣ በሻዓልቢም፣በቤትሳሜስ፣ በኤሎንቤትሐናን፤ 10ቤንሔሴድ፣ በአሩቦት ውስጥየሚገኙት ሰኰትና የኦፌር አገርበሙሉ የእርሱ ነበር፤ 11ቤን አሚናዳብ፤ በናፎትረ ዶር፣እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ጣፈትንአግብቶ የነበረ ነው፤ 12የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክናበመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለውበቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምንተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣ 13ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማእዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንምየአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ሥልሳባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤ 14የዒዶ ልጅ አሒናዳብ፤ በማሃናይም፣ 15አኪማአስ በንፍታሌም፣ እርሱምየሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶየነበረ ነው፤ 16የኩሲ ልጅ በዓና፤ በአሴርና በበዓሎት፣ 17የፋሩዋ ልጅ ኢዮሣፍጥ በይሳኮር፣ 18የኤላ ልጅ ሳሚ በብንያም፣ 19የኡሪ ልጅ ጌበር፤በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፣ እርሱምየአውራጃው ብቸኛ ገዥ ነበር።

ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለት ቀለብ

20የይሁዳና የእስራኤል ሕዝቦች ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሆነ፤ ይበሉ፣ ይጠጡና ይደሰቱም ነበር። 21ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብፅ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት። 22ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለትም ቀለብ ይህ ነበር፤ ሠላሳ ኮር ማለፊያ ዱቄት፣ ሥልሳ ኮር መናኛ ዱቄት፣ 23ዐሥር ቅልብ ሰንጋዎች፣ ሃያ ግጦሽ መሬት ላይ የሚውሉ በሬዎች፣ መቶ በግና ፍየል እንዲሁም ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ የበረሓ ፍየልና ምርጥ አዕዋፍ። 24ከወንዙ በስተ ምዕራብ፣ ከቲፍሳ እስከ ጋዛ ያሉትን መንግሥታት ስለ ገዛ፣ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ሆኖለት ነበር። 25በሰሎሞን ዘመን ሁሉ ከዳን አንሥቶ እስከ ቤርሳቤህ ያለው ይሁዳና እስራኤል፣ እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለሱ ጥላ ሥር በሰላም ለመኖር በቃ። 26ሰሎሞን ሠረገላ የሚጐትቱ ፈረሶች የሚያድሩበት አራት ሺህ ጋጣና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት። 27የየአውራጃው ሹማምትም በየወር ተራቸው ንጉሡን ሰሎሞንንና ወደ ንጉሡ ማእድ የሚቀርቡትን ሁሉ ምንም ሳያጓድሉ ይቀልቡ ነበር፤ 28እንዲሁም ለሠረገላ ፈረሶችና ለፈጣን ፈረሶች የተመደበውን ገብስና ጭድ ከተፈለገው ቦታ ድረስ ያመጡ ነበር።

የሰሎሞን ጥበብ

29አምላክ ለሰሎሞን ጥበብንና እጅግ ታላቅ ማስተዋልን እንዲሁም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋትን ሰጠው። 30የሰሎሞን ጥበብ ከምሥራቅ ሰዎች ሁሉ ጥበብ በጣም የላቀ ከግብፅም ጥበብ ሁሉ የበለጠ ነበር፤ 31እርሱም ከማንም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር፣ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታን፣ ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ደግሞም ከደራል ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አሕዛብ ሁሉ ተሰማ። 32እርሱም ሦስት ሺህ ምሳሌዎችን ተናገረ፤ የመሓልዩም ቍጥር ሺህ አምስት ነበር። 33ከሊባኖስ ዝግባ አንሥቶ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ስለ ዕፀዋት ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በሆዳቸው ስለሚሳቡ እንስሳትና ስለ ዓሦችም ተናግሮአል፤ 34ጥበቡን ከሰሙት ከዓለም ነገሥታት ሁሉ የተላኩ፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ የሰሎሞንን ጥበብ ለማድመጥ መጡ።