39 ከዚህ የተነሣም የዳዊትን ቤት አዋርዳለሁ፤ ነገር ግን ለዘላለም አይደለም።’ ”
40 ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ፈለገ፤ ኢዮርብዓም ግን ወደ ግብፅ ሸሸ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሺሻቅ ሄዶ፣ ሰሎሞን እስኪሞት ድረስ በዚያው ተቀመጠ።
41 የቀረው በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት የተከናወነው፣ የሠራውም ሁሉ፣ ጥበቡም በሰሎሞን የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎ የለምን?
42 ሰሎሞን በመላው እስራኤል ላይ በኢየሩሳሌም የነገሠው አርባ ዓመት ነው።
43 ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።