2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ከንጉሥ ሰሎሞን ሸሽቶ ከሚኖርበት ከግብፅ ተመልሶ መጣ።
3 ስለዚህም ወደ ኢዮርብዓም ላኩበት፤ እርሱና መላው የእስራኤል ጉባኤም ወደ ሮብዓም መጥተው፣
4 “አባትህ ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን አሁን የአባትህን የጭካኔ አገዛዝ የጫነብንንም ከባድ ቀንበር ብታቀልልን እንገዛልሃለን” አሉት።
5 ሮብዓምም፣ “እንግዲያውስ ሂዱ፤ ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው። ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ።
6 ከዚያም ሮብዓም አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ ካገለገሉት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ፤ “ለዚህ ሕዝብ ምን መልስ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” አላቸው።
7 እነርሱም፣ “ዛሬ አንተ ለዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆን፣ ብትገዛለትና ደስ የሚያሰኝ መልስ ብትሰጠው፣ ምንጊዜም የአንተ አገልጋይ ይሆናል” ብለው መለሱለት።
8 ሮብዓም ግን ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ንቆ፣ አብሮ አደግ የሆኑትንና እርሱን የሚያገለግሉትን ወጣቶች፣