1 ነገሥት 12:4-10 NASV

4 “አባትህ ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን አሁን የአባትህን የጭካኔ አገዛዝ የጫነብንንም ከባድ ቀንበር ብታቀልልን እንገዛልሃለን” አሉት።

5 ሮብዓምም፣ “እንግዲያውስ ሂዱ፤ ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው። ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ።

6 ከዚያም ሮብዓም አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ ካገለገሉት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ፤ “ለዚህ ሕዝብ ምን መልስ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” አላቸው።

7 እነርሱም፣ “ዛሬ አንተ ለዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆን፣ ብትገዛለትና ደስ የሚያሰኝ መልስ ብትሰጠው፣ ምንጊዜም የአንተ አገልጋይ ይሆናል” ብለው መለሱለት።

8 ሮብዓም ግን ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ንቆ፣ አብሮ አደግ የሆኑትንና እርሱን የሚያገለግሉትን ወጣቶች፣

9 “ሐሳብ ለማግኘት፣ የእናንተስ ምክር ምንድን ነው? ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች ምን መልስ እንስጥ?” ሲል ጠየቃቸው።

10 ወጣት አብሮ አደጎቹም፣ እንዲህ አሉት፣ “ ‘አባትህ ከባድ ቀንበር ጫነብን፣ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ላሉህ ለእነዚህ ሰዎች፣ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤