1 ነገሥት 12:8-14 NASV

8 ሮብዓም ግን ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ንቆ፣ አብሮ አደግ የሆኑትንና እርሱን የሚያገለግሉትን ወጣቶች፣

9 “ሐሳብ ለማግኘት፣ የእናንተስ ምክር ምንድን ነው? ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች ምን መልስ እንስጥ?” ሲል ጠየቃቸው።

10 ወጣት አብሮ አደጎቹም፣ እንዲህ አሉት፣ “ ‘አባትህ ከባድ ቀንበር ጫነብን፣ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ላሉህ ለእነዚህ ሰዎች፣ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤

11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን ከዚያ ይብስ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ’ በላቸው!” አሉ።

12 ንጉሡ፣ “በሦስተኛው ቀን ተመልሳችሁ ኑ” ብሎአቸው ስለ ነበር፣ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም ተመልሰው መጡ።

13 ንጉሡም በሽማግሌዎቹ የተሰጠውን ምክር ትቶ፣ ሕዝቡን የሚያስከፋ መልስ ሰጣቸው፤

14 ወጣቶቹ የሰጡትን ምክርም ተቀብሎ፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ ከዚያ ይብስ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገረፋችሁ፣ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።