1 ነገሥት 14:20-26 NASV

20 እርሱም ሃያ ሁለት ዓመት ነግሦ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁ ናዳብም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

21 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ ነገሠ፤ በነገሠም ጊዜ ዕድሜው አርባ አንድ ዓመት ነበር፤ እርሱም እግዚአብሔር ለስሙ መጠሪያ እንድትሆን ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጣት በኢየሩሳሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ። እናቱ ናዕማ የተባለች አሞናዊት ነበረች።

22 ይሁዳ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ ከአባቶቻቸው ይልቅ እነርሱ በሠሩት ኀጢአት ይበልጥ የቅናት ቊጣውን አነሣሡ፤

23 እንዲሁም በእያንዳንዱ ኰረብታና በየትልልቁ ዛፍ ጥላ ሥር የማምለኪያ ኰረብቶችን አዕማደ ጣዖታት፣ የአሼራን ምስል ዐምድ ለራሳቸው አቆሙ።

24 ከዚያም ይልቅ፣ የቤተ ጣዖት ወንደቃዎች በምድሪቱ ላይ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት አሳዶ ያስወጣቸው አሕዛብ የፈጸሙትን አስጸያፊ ድርጊት ሁሉ እነዚህም ፈጸሙ።

25 ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ፤

26 የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ወሰደ፤ ሰሎሞን ያሠራቸው የወርቅ ጋሻዎች እንኳን ሳይቀሩ ሁሉንም ነገር አጋዘ።