1 ንጉሥ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤
2 ዋና ዋናዎቹ ሹማምቱም እነዚህ ነበሩ፤የሳዶቅ ልጅ ዓዛርያስ፣ ካህን፤
3 የሺሻ ልጆች ኤሊሖሬፍናአኪያ፣ ጸሓፊዎች፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣ ታሪክ ጸሓፊ፤
4 የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ የሰራዊቱ ዋና አዛዥ፤ሳዶቅና አብያታር፣ ካህናት፤
5 የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃገዦች የበላይ ኀላፊ፤የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡየቅርብ አማካሪ፤
6 አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራተቈጣጣሪ።