6 አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራተቈጣጣሪ።
7 እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ።
8 ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ቤንሑር፣ በኰረብታማው በኤፍሬምምድር፤
9 ቤንጼቄር፣ በማቃጽ፣ በሻዓልቢም፣በቤትሳሜስ፣ በኤሎንቤትሐናን፤
10 ቤንሔሴድ፣ በአሩቦት ውስጥየሚገኙት ሰኰትና የኦፌር አገርበሙሉ የእርሱ ነበር፤
11 ቤን አሚናዳብ፤ በናፎትረ ዶር፣እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ጣፈትንአግብቶ የነበረ ነው፤
12 የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክናበመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለውበቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምንተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣