2 ነገሥት 19:3-9 NASV

3 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ የሚለው ይህ ነው፤ ‘እንግዲህ ይህች ዕለት የመከራ፣ የዘለፋና የውርደት ቀን ናት፤ ይህችም ቀን ልጆች ሊወለዱ ምጥ እንዳፋፋመበት፣ ነገር ግን ለመገላገል ዐቅም እንደታጣበት ሰዓት ናት።

4 ሕያው እግዚአብሔርን ያንቋሽሽ ዘንድ በጌታው በአሦር ንጉሥ የተላከውን የጦር አዛዡን ቃል ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ሰምቶ ይሆናልና፣ ስለሰማውም ቃል እግዚአብሔር እንዲገሥጸው በሕይወት ስለተረፉት ወገኖቻችን እባክህ ጸልይ።”

5 የንጉሥ ሕዝቅያስ ሹማምት ወደ ኢሳይያስ በመጡ ጊዜ፣

6 ኢሳይያስ እንዲህ አላቸው፤ “ለጌታችሁ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ ‘እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች በእኔ ላይ የወረወሯቸውን የስድብ ቃላት በመስማትህ አትፍራ።

7 እነሆ፣ አንድ ዐይነት መንፈስ አሳድርበታለሁ፤ የሆነ ወሬም ሲሰማ ወደ አገሩ ይመለሳል፤ እዚያም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ።’ ”

8 የጦር አዛዡም የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ትቶ መሄዱን ሲሰማ ተመለሰ፤ ንጉሡንም ልብናን ሲወጋ አገኘው።

9 በዚህም ጊዜ የግብፅ ንጉሥ ኢትዮጵያዊው ቲርሐቅ፣ ሊወጋው በመገሥገሥ ላይ መሆኑን ሰናክሬም ሰማ፤ ስለዚህ ወደ ሕዝቅያስ እንደ ገና እንዲህ ሲል መልእክተኞች ላከ፤