2 ነገሥት 20:1-6 NASV

1 በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ሊሞት ተቃርቦ ነበር። የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እግዚአብሔር፣ ‘ትሞታለህ ከእንግዲህ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል’ ብሎሃል” አለው።

2 ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤

3 “እግዚአብሔር ሆይ፤ በታማኝነትና በፍጹም ልብ በፊትህ እንደሄድሁ፣ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ አስብ፤” ሕዝቅያስም ምርር ብሎ አለቀሰ።

4 ኢሳይያስ የመካከለኛውን አደባባይ አልፎ ከመሄዱ በፊት የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤

5 “ተመለስና የሕዝቤን አለቃ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፤ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፣ እፈውስሃለሁ። ከዛሬ ሦስት ቀን በኋላ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፤

6 በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ ስለ ራሴና ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊት ስል ይህችን ከተማ እከላከልላታለሁ።’ ”