1 ምናሴ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐፍሴባ ትባል ነበር።
2 ምናሴ እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት አሳዶ ያወጣቸውን የአሕዛብን አስጸያፊ ልማድ በመከተል በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ።
3 አባቱ ሕዝቅያስ ያፈረሰውን የየኰረብታውን ማምለኪያ ስፍራ መልሶ ሠራ፤ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም ለበኣል መሠዊያዎችን አቆመ፤ የአሼራንም ምስል ዐምድ ሠራ። እንዲሁም ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።
4 እግዚአብሔር፣ “ስሜን በኢየሩሳሌም አኖራለሁ” ባለበት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠዊያዎችን ሠራ።
5 በሁለቱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባዮች ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊት ሁሉ መሠዊያ ሠራ።