3 ከመካከላቸውም አንዱ፣ “አንተስ ከአገልጋዮችህ ጋር አትመጣምን?” አለው።ኤልሳዕም፣ “እሺ እሄዳለሁ” አለ፤
4 አብሮአቸውም ሄደ። ወደ ዮርዳኖስም ሄደው ዛፎች መቊረጥ ጀመሩ።
5 ከእነርሱም አንዱ ዛፍ እየቈረጠ ሳለ፣ መጥረቢያው በሮ ከውሃው ውስጥ ወደቀ፤ እርሱም፣ “አየ ጒድ ጌታዬ፤ የተውሶ መጥረቢያ እኮ ነው!” ብሎ ጮኸ።
6 የእግዚአብሔርም ሰው፣ “በየት በኩል ነው የወደቀው?” ሲል ጠየቀ። ቦታውን ባሳየውም ጊዜ ኤልሳዕ እንጨት ቈርጦ ወደ ውሃው ውስጥ በመጣል መጥረቢያውን እንዲንሳፈፍ አደረገው።
7 ከዚያም፣ “በል አውጣና ውሰደው” አለው፤ ሰውየውም እጁን ዘርግቶ ወሰደው።
8 በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ይዋጋ ነበር፤ ከጦር አለቆቹ ጋር ከተመካከረ በኋላም፣ “በዚህ፣ በዚህ ቦታ እሰፍራለሁ” አለ።
9 የእግዚአብሔርም ሰው፣ “ሶርያውያን በዚያ ታች ወርደዋልና በዚያ በኩል እንዳታልፍ ተጠንቀቅ” ሲል ለእስራኤል ንጉሥ ላከበት።