2 ዜና መዋዕል 21:14-20 NASV

14 ስለዚህ እነሆ፤ እግዚአብሔር ሕዝብህን፣ ልጆችህን፣ ሚስቶችህንና ያለህን ሁሉ በታላቅ መቅሠፍት ይመታል።

15 አንተም ራስህ በየዕለቱ እየባሰ በሚሄድ የአንጀት በሽታ ክፉኛ ትታመማለህ፤ በመጨረሻም ሕመሙ አንጀትህን ወደ ውጭ ያወጣዋል።”

16 እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩ ዐረቦችን በኢዮሆራም ላይ በጠላትነት እንዲነሡ አደረገ።

17 እነርሱም በይሁዳ ላይ ወጡ፤ ወረሯትም። በንጉሡ ቤተ መንግሥት የሚገኘውን ዕቃ ሁሉ፣ ከወንዶች ልጆቹና ከሚስቶቹ ጋር ወሰዱ፤ ከመጨረሻ ልጁ ከአካዝያስ በስተቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም።

18 ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር ሊድን በማይችል የአንጀት በሽታ ኢዮሆራምን ቀሠፈው።

19 ሕመሙም ሲያሠቃየው ከቈየ በኋላ፣ በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ በዚሁ ሳቢያ አንጀቱ ወጥቶ በከባድ ሥቃይ ሞተ። ሕዝቡም ለአባቶቹ ክብር እሳት ያነድዱ ነበር፤ ለእርሱ ግን አላነደዱለትም።

20 ኢዮሆራም ሲነግሥ ዕድሜው ሠላሳ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ስምንት ዓመት ገዛ። በሞተ ጊዜም ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊትም ከተማ እንጂ በነገሥታቱ መቃብር አልቀበሩትም።