9 ሐቀኛ ሰው ያለ ሥጋት ይራመዳል፤በጠማማ ጐዳና የሚሄድ ግን ይጋለጣል።
10 በተንኰለኛ ዐይን የሚጠቅስ ሐዘን ያስከትላል፤ለፍላፊ ተላላም ወደ ጥፋት ያመራል።
11 የጻድቅ አንደበት የሕይወት ምንጭ ናት፤መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።
12 ጥላቻ ጠብን ያነሣሣል፤ፍቅር ግን ስሕተትን ሁሉ ይሸፍናል።
13 ጥበብ በአስተዋይ ሰው ከንፈር ትገኛለች፤በትር ግን ማመዛዘን ለጐደለው ሰው ጀርባ ነው።
14 ጠቢባን ዕውቀት ያከማቻሉ፤የተላላ አንደበት ግን ጥፋትን ይጋብዛል።
15 የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ድኽነት ግን የድኾች መጥፊያ ናት።