1 እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሰኘዋል።
2 ትዕቢት ስትመጣ ውርደትም ትከተላለች፤በትሑት ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።
3 ቅኖችን ትክክለኛነታቸው ትመራቸዋለች፤ወስላቶች ግን በገዛ አታላይነታቸው ይጠፋሉ።
4 በቊጣ ቀን ሀብት ፋይዳ የለውም፤ጽድቅ ግን ከሞት ትታደጋለች።