15 ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራ ያገኘዋል፤ዋስትና ለመስጠት እጅ የማይመታ ግን ምንም አይደርስበትም።
16 ርኅሩኅ ሴት ክብር ታገኛለች፤ጒልበተኛ ሰዎች ግን ብልጽግናን ብቻ ያገኛሉ።
17 ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ጨካኝ ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል።
18 ክፉ ሰው የሚያገኘው ትርፍ መቅኖ የለውም፤ጽድቅን የሚዘራ ግን አስተማማኝ ዋጋ ያገኛል።
19 እውነተኛ ጻድቅ ሕይወትን ያገኛል፤ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞቱ ይጓዛል።
20 እግዚአብሔር ልበ ጠማሞችን ይጸየፋል፤በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል።
21 ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ።