25 ለጋስ ይበለጽጋል፤ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል።
26 በድብቅ እህል የሚያከማቸውን ሕዝብ ይረግመዋል፤አውጥቶ የሚሸጥ ግን በረከት ይጐናጸፋል።
27 በጎ ነገርን ተግቶ የሚሻ በጎ ነገር ይጠብቀዋል፤ክፉ ነገር የሚፈልገውን ግን ክፉ ያገኘዋል።
28 በሀብቱ የሚታመን ሁሉ ይወድቃል፤ጻድቃን ግን እንደ አረንጓዴ ቅጠል ይለመልማሉ።
29 ቤተ ሰቡን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፤ተላላም ሰው የጠቢብ ሎሌ ይሆናል።
30 የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፤ነፍሳትን የሚማርክም ጠቢብ ነው።