15 ተላላ ሰው መንገዱ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤ጠቢብ ሰው ግን ምክር ይሰማል።
16 ተላላ ሰው ቊጣው ወዲያውኑ ይታወቅበታል፤አስተዋይ ሰው ግን ስድብን ንቆ ይተዋል።
17 ሐቀኛ ምስክር በእውነት ይመሰክራል፤ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸት ይናገራል።
18 ግድ የለሽ ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤የጠቢብ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል።
19 እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።
20 ክፋትን በሚያውጠነጥኑ ሰዎች ልብ አታላይነት አለ፤ሰላምን የሚያራምዱ ግን ደስታ አላቸው።
21 ጻድቃን ጒዳት አያገኛቸውም፤ክፉዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው።