3 ሰው በክፋት ላይ ተመሥርቶ ሊጸና አይችልም፤ጻድቃን ግን ከቦታቸው አይነቃነቁም።
4 መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።
5 የጻድቃን ሐሳብ ቀና ነው፤የክፉዎች ምክር ግን ሸር አለበት።
6 የክፉዎች ቃል ደም ለማፍሰስ ታደባለች፤የቅኖች ንግግር ግን ይታደጋቸዋል።
7 ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፤ ድራሻቸውም ይጠፋል፤የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።
8 ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፤ጠማማ ልብ ያላቸው ግን የተናቁ ናቸው።
9 የሚበላው ሳይኖረው ከሚኵራራ ይልቅ፣ራሱን ዝቅ አድርጎ ሠራተኛ የሚያሳድር ይሻላል።