1 ጠቢብ ልጅ የአባቱን ምክር በማስተዋል ይሰማል፤ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አያዳምጥም።
2 ሰው ከከንፈሩ ፍሬ መልካም ነገር ያገኛል፤ወስላቶች ግን ዐመፅን ይናፍቃሉ።
3 አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል።
4 ሰነፍ አጥብቆ ይመኛል፤ አንዳችም አያገኝም፤የትጉዎች ምኞት ግን ይረካል።
5 ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ክፉ ሰው ግን ኀፍረትንና ውርደትን ያመጣል።