5 ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ክፉ ሰው ግን ኀፍረትንና ውርደትን ያመጣል።
6 ጽድቅ ቅን የሆነውን ሰው ትጠብቀዋለች፤ክፋት ግን ኀጢአተኛውን ትጥለዋለች።
7 ምንም ሳይኖረው ባለጠጋ መስሎ የሚታይ ሰው አለ፤ሌላው ድኻ መስሎ ይታያል፤ ግን ብዙ ሀብት አለው።
8 የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።
9 የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።
10 ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።
11 ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል።