8 የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።
9 የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል።
10 ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።
11 ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል።
12 ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል፤የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።
13 ምክርን የሚያቃልል በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል፤ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ይቀበላል።
14 የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ሰውን በሞት ወጥመድ እንዳይያዝ ታደርገዋለች።