16 ጠቢብ ሰው ጥንቁቅ ነው፤ ከክፉም ይርቃል፤ተላላ ግን ችኵልና ደንታ ቢስ ነው።
17 ግልፍተኛ ሰው የቂል ተግባር ይፈጽማል፤መሠሪም ሰው አይወደድም።
18 ብስለት የሌላቸው ተላላነትን ይወርሳሉ፤አስተዋዮች ግን ዕውቀትን እንደ ዘውድ ይጭናሉ።
19 ክፉዎች በደጎች ፊት፣ኀጥኣንም በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።
20 ድኾችን ወዳጆቻቸው እንኳ ይጠሏቸዋል፤ባለጠጎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው።
21 ጎረቤቱን የሚንቅ ኀጢአት ይሠራል፤ለተቸገሩት የሚራራ ግን ቡሩክ ነው።
22 ክፉ ነገር የሚያቅዱ ከትክክለኛው መንገድ ይወጡ የለምን?በጎ ነገር የሚያቅዱ ግን ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።