19 ክፉዎች በደጎች ፊት፣ኀጥኣንም በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።
20 ድኾችን ወዳጆቻቸው እንኳ ይጠሏቸዋል፤ባለጠጎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው።
21 ጎረቤቱን የሚንቅ ኀጢአት ይሠራል፤ለተቸገሩት የሚራራ ግን ቡሩክ ነው።
22 ክፉ ነገር የሚያቅዱ ከትክክለኛው መንገድ ይወጡ የለምን?በጎ ነገር የሚያቅዱ ግን ፍቅርንና ታማኝነትን ያተርፋሉ።
23 ለፍተው የሠሩት ሁሉ ትርፍ ያስገኛል፤ከንቱ ወሬ ግን ወደ ድኽነት ያመራል።
24 ጠቢባን ብልጥግና ዘውዳቸው ነው፤የተላሎች ተላላነት ግን ፍሬው ከንቱነት ነው።
25 እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፤ሐሰተኛ ምስክር ግን አባይ ነው።