24 ጠቢባን ብልጥግና ዘውዳቸው ነው፤የተላሎች ተላላነት ግን ፍሬው ከንቱነት ነው።
25 እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፤ሐሰተኛ ምስክር ግን አባይ ነው።
26 እግዚአብሔርን የሚፈራ ጽኑ አምባ አለው፤ልጆቹም መጠጊያ ይኖራቸዋል።
27 እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል።
28 የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ክብር ሲሆን፣የዜጐች ማነስ ግን ለገዥ መጥፊያው ነው።
29 ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ይገልጣል።
30 ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ቅናት ግን ዐጥንትን ያነቅዛል።