7 ከተላላ ሰው ራቅ፤ከከንፈሮቹ ዕውቀት አታገኝምና።
8 የአስተዋዮች ጥበብ መንገዳቸውን ልብ ማለት ነው፤የተላሎች ሞኝነት ግን መታለል ነው።
9 ተላሎች በሚያቀርቡት የበደል ካሳ ያፌዛሉ፤በቅኖች መካከል ግን በጎ ፈቃድ ትገኛለች።
10 እያንዳንዱ ልብ የራሱን መራራ ሐዘን ያውቃል፤ደስታውንም ማንም ሊጋራው አይችልም።
11 የክፉዎች ቤት ይፈርሳል፤የቅኖች ድንኳን ግን ይስፋፋል።
12 ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ያደርሳል።
13 በሣቅ ጊዜ እንኳ ልብ ይተክዛል፤ደስታም በሐዘን ሊፈጸም ይችላል።