2 ጠቢብ አገልጋይ በወራዳ ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ከወንድማማቾቹም እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።
3 ማቅለጫ ለብር፣ ከውር ለወርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመረምራል።
4 እኵይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።
5 በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤በሌላው ሰው መከራ ደስ የሚለው ከቅጣት አያመልጥም።
6 የልጅ ልጆች ለአረጋውያን ዘውድ ናቸው፤ወላጆችም ለልጆቻቸው አለኝታ ናቸው።
7 መልካም አነጋገር ለተላላ አይሰምርለትም፤ለገዥማ ሐሰተኛ አንደበት የቱን ያህል የከፋ ይሆል!
8 እጅ መንሻ ለሰጭው እንደ ድግምት ዕቃ ነው፤በሄደበትም ቦታ ሁሉ ይሳካለታል።