1 ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ቅን የሆነውን ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።
2 ተላላ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል።
3 ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ከዕፍረትም ጋር ውርደት ትመጣለች።
4 ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።